free-photo-of-cozy-dessert-with-chocolate-and-tea

Customer Service በኢትዮጵያ

በሃገራችን የቢዝነስ trend ውስጥ እጅግ ጎልቶ የሚታየው ጉድለት ቢኖር Customer Service (የደምበኛ አያያዝ ነው)። ይህ ችግር ትኩረት ያለተሰጠው ተብሎ ብቻ ሊታለፍ የማይችል በብዙ የቢዝነስ ተቋማት በጣም በወረደ ደረጃ ላይ ያለ ነው።

ይህን ችግር ተረድቶ የተለየ የCustomer Service Strategy ቀርጾ በአስደሳች የደምበኛ አያያዝ መምጣት ለሚፈልግ Startup businessም ሆነ ነባር ቢዝነስ እጅግ አጓጊ የሆነ የቢዝነስ እድል ነው። ምክንያቱም ጥሩ የደምበኛ አያያዝ ያለው የቢዝነስ ተቋም ማግኘት ብርቅ በሆነበት አገር የተለየ customer service ይዘህ ብትመጣ ገበያውን መቆጣጠር የምትችልበት ወርቃማ የቢዝነስ እድል ነው።

ይህ አገላለጽ የተጋነነ ቢመስልም ግን ተጨባጭ እውነታ ነው። በሃገራችን customer service ትኩረት የተነፈገው ጉዳይ ከመሆኑ የተነሳ ደምበኞች ገንዘባቸውን ከፍለው የሚጉላሉበት ክስተት ሰው እየተለማመደው በመምጣቱ እንደ ቅቡል ነገር የወሰደው ይመስላል። ይህንን trend (ልማድ) ለመስበር ደፍሮ በተለየ የcustomer Service ስትራቴጂ መመጣት የቻለ ቢዝነስ ያለ ጥርጥር Competitive Advantage ይኖረዋል።

ይህን በምሳሌ እንየው፡ –

የሆነ አንድ ስብሰባ ለመሳተፍ ከስብሰባ በፊት ባለችህ ትንሽ ደቂቃ ቡና ጠጥተህ ነቃ ብለህ በጥሩ ስሜት መግባት ፈልገሃል እንበል። የሆነ ካፌ ጎራ ትላለህ። ቡና ለማዘዝ ቁጭ ብለሃል። ያለህ ደቂቃ ትንሽ ስለሆነ ቸኩለሃል።  እስካሁን ምን ልታዘዝ ብሎ የመጣ የለም። ከደቂቃዎች በኋላ ፊቱን አኮሳትሮ ይታዘዝሃል። ቡናህ እስኪደርስ እየተቁነጠነጥክ ትጠብቃለህ። ቡናው ከስንት ጥበቃ በኋላ መጣልህ። ቡናውን ቶሎ ጠጥተህ ሂሳብ ለመክፈል እንደገና ማጨብጨብና መጠበቅ ይኖርብሃል። “ይቅርታ መብራት ስለጠፋ ኮምፒዩተሩ ጠፍቷል፣ ትንሽ ጠብቅ ጀነሬተር እሲኪበራ” ትባላለህ። ሰዓት አልፎብሃል። ሳትከፍል ደግሞ መውጣት አትችልም። ለመከፈል ደግሞ መብራት መምጣት አለበት፣ receipt መቆረጥ አለበት ይሉሃል። ለዚህ ይቅርታ የሚጠይቅህ እንኳ የለም። በዚህ መልኩ በተበላሸ ስሜት ሰዓት አሳልፈህ ወደ ስብሰባህ ትገባለህ።

ከዛች ቀን በኋላ እዛ ካፌ ላለመግባት ትወስናለህ። ግን ብዙ ካፌዎች ያላቸው customer Service ከዚህ ብዙም የተሻለ አይደለም። ሰው ገንዘቡን ከፍሎ መጉላላትን ለምዶታል። ደምበኛን መንከባከብ ብዙዎቹ ጋር የማይታሰብ ነው።

የቢዝነስ እድል ያለው እዚህ ጋር ነው። በተለየ የcustomer Service ስትራቴጂ ደምበኞችን ማሰተናገድ የምትችልበት ጥበብ ይዘህ ከመጣህ ያለ ጥርጥር competitive advantage ይኖርሃል።

ሌላው በ customer አያያዝ ሰፊ ክፍተት ከሚታይባቸው የሃገራችን የቢዝነስ ሴክተሮች ውስጥ የጤና ተቋማት አንዱ ናቸው። የታመመ፣ ወይም ሰው የታመመበት ሰው በጭንቀት ውስጥ ስለሚሆን የተለየ የcustomer Service ያስፈልገዋል፡ ይሁን እንጂ እጅግ በጣም ጥቂት ቁጥር ካላቸው ተቋማት በስተቀር በብዙዎቹ የጤና ተቋማት ያለው የcustomer Service አሳዛኝ  ነው። ይህም በግል የጤና የቢዝነስ ተቋማትም በሰፊው የሚታይ ችግር ነው። ከካርድ ክፍል ጀምሮ ነርሶችም ላብራቶሪ ከፍልም፣ ሂሳብ ክፍልም፣ ጥበቃዎችም ሁሉም ሲያመናጭቁህ እና ሲኮሳተሩብህ ማየት በኛ አገር እንግዳ ነገር አይደለም። ሰውም እንደ normal ነገር የተቀበለው ይመስላል። አብዛኛው ተገልጋይ እንደውም ከፍሎ ለሚያገኘው አገልግሎት የመለማመጥና የመሳቀቅ ግዴታ እንዳለበት አድርጎ የተቀበለው ይመስላል።

ይህንን trend የሚቀይር ፍጹም እንክብካቤ የተሞላበት የcustomer Service የሚሰጥበት የጤና ተቋም ቢዝነስ መፍጠር ብትችል  ያለ ጥርጥር Competitive Advantage የምታገኝበት ሌላ የbusiness opportunity ነው። በተለይ በጤና ተቋማት  customer Service እጅግ ወሳኝ ከመሆኑ የተነሳ ታክሞ ህመሙ ብሶበት፣ ወይም ሳይታከም እንኳን ተሽሎት እንዲሄድ የማድረግ ያህል አቅም ያለው ነው።

ከነዚህ ሁሉ መረዳት የምንችለው ኢትዮጵያ ውስጥ በቀላሉ የቢዝነስ Competitive Advantage የምናገኝበት እድል ቢኖር Customer Service ነው።

ስለዚህ የተዋጣለት የCustomer Service ስትራቴጂ ቅረጽ እና ይህን እድል ተጠቅመህ በቢዝነስህ ውጤታማ ሁን።

Author:  Semira Temam,

Customer Services Manager and Trainer

@ Zafer Plus Business and Investment Consultancy Services

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *