Top view desk of work table in office with laptop computer , notebook , calculator and a cup of coffee for creative business work or marketing plan to success planning of company

ገበያን የመፍጠር ጥበብ

ካቆምንበት እንድንቀጥል ‘ገበያን መፈለግ ወይስ ገበያን መፍጠር?’ የሚለውን ጽሑፌን አንብባችሁ እንደሆነ ላስብና ልቀጥል . . .

ገበያን የመፍጠር ጥበብ እንዴት ያንተን እና የሌሎች ሺዎች ሂወት ልትቀይርበት እንደምትችል አንድ ምሳሌ አንስተን እንይ፦
ስታርባክስ ከዓመታት በፊት አንድ ትንሽዬ ቡና መሸጫ ካፌ ነበረች። አሁን በመላው ዓለም ከ33800 በላይ ቅርጫፍ ካፌዎች ያሉት የዓለማችን ብቸኛ ግዙፍ እና ተውዳጅ ትኩስ ቡና መሸጫ ኩባንያ ነው። ከአሜሪካ እስከ አውሮፓ ከእስያ እስከ አፍሪካ የስታርባክስ ቡና ሚሊዮኖች ጠጥተው ይነቁበታል። ዝርዝሩን እንተወውና በጥቂት ዓመታት ውስጥ ይህ ተዓምር እንዴት ሊፈጠር እንደቻለ እንይ፦ የዚህ ተዓምር ፈጣሪ ሃዋርድ ሹልትዝ ነው። በሌላ አይደለም – ገበያን በመፍጠር ጥበብ ነው።
ሃዋርድ ሹልትዝ የትንሽዋ ስታር ባክስ ካፌ ከሌሎች ሁለት ሰዎች ጋር ለሶስት በጋራ ባለቤት ሆነው ይሰሩ ነበር። ሹልትዝ ግን በግሉም በአንድ የቤት እቃዎች አቅራቢ ድርጅት ውስጥ የማርኬቲንግ ባለሙያ ሆኖ ይሰራ ነበር። በአንድ አጋጣሚ ኩባንያው ለስራ ጉዳይ ወደ ጣሊያን አገር ይልከዋል። ጣሊያን በሄደበት አጋጣሚ አንድ ነገር ታዘበ። ጣሊያኖች ቡና የመጠጣት ባህላቸው ከፍተኛ እንደሆነ አስተውሏል። በወቅቱ በሚላን ከተማ ብቻ ከ1,500 በላይ የቡና መሸጫ ካፌዎች እንደነበሩ ተገንዝቧል። በዚህም አንድ ሃሳብ መጣለት። ይህ ተወዳጅ የሆነው እና በካፕችኖ መልክ የሚዘጋጀው የጣሊያኖች የቡና አሰራር በሃገሩ አሜሪካ ማስተዋወቅ ቢችል ትልቅ ገበያ እንደሚፈጥርና ራሱን እና ሚሊዮኖችን መቀየር እንደሚችል ገባው። ልክ ወደ ሃገሩ እንደተመለሰ ይህንን ሃሳብ ለስራ አጋሮቹ አጋራቸው። እነሱ ግን አልተቀበሉትም። ከተለመደው የቡና አሰራር ውጪ መሞከር ያሉትን ደንበኞች ማባረር ሆኖ ተሰማቸው። በዚህ ምክንያት ሹልትዝ ከነሱ ተለይቶ የራሱን ካፌ በመክፈት አዲስ የቡና አፈላል ባህል በማስተዋወቅ አዲስ ገበያን መፍጠሩን ተያያዘው። ብሮሸሮችን አዘጋጅቶ ለስራ በጥዋት የሚጣደፉትን አሜሪካውያን በአዲሱ ቡና ተነቃቅተው እንዲገቡ ቀሰቀሰ። በዚህም በአራት አመት ውስጥ በከተማው ከ100 በላይ ካፌዎችን ለመክፈትና ዓለምን ለማነጋገር በቃ። እነዛ ትንሽዋን ስታርባክስ ካፌ ይዘው የቀሩት ጓድኞቹ በተለመደው ገበያን የመፈለግ ሂደት ብዙም ሳይለወጡ ቁጭ ብለው ጠበቁት። ሹልትዝ ስታርባክስ የሚለው ስሟ ይፈልገው ስለነበር ይህን ስም ከነሱ ገዝቶ በተለመደው ገበያን የመፍጠር ጥበቡ እድገቱን ተያያዘው። በአሁኑ ሰአት ስታርባክስ በ5ቱም ከፍላተ ዓለማት በ80 ሃገራት 33,833 የቡና መሸጫ ካፌዎች ያሉት ግዙፍ ኩባንያ ለመሆን በቅቷል፡፡ ይህ የሆነው ደግሞ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ነው። ገበያን የመፍጠር ጥበብ የፈጠረው ተአምር።

ከዚህ ምን ተማርክ? የተለመደው ገበያን የመፈለግ ሂደት ብዙ ርቀት አያስኬድህም። ቢያስኬድህም በዔሊ ፍጥነት ነው። ስለዚህ አእምሮህን አሰራውና አዲስ ፈጠራ ተጠቅመህ አዲስ ገበያን ፍጠር። ገበያን በመፍጠር ብቁ ከሆንክ በርግጠኝነት ባለህ ነገር ላይ ውጤታማ ትሆናለህ። ተዓምር ትፈጥራለህ።
© ሙስጦፋ አብደላ

በ 0929296992 ይደውሉ።

Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *