እንደ ሰው በምትፈልገው ነገር ላይ ስኬታማ ለመሆንና ትልቅ ደረጃ ለመድረስ የተሻለው መንገድ የቱ ነው? Business Specialization ወይስ Business Generalization?
አንተ በንግዱ አለም የተሰማራህ ሰው ነህ እንበል። በአጭር ጊዜ ውስጥ ስኬታማ ለመሆን የሚያስችልህ መንገድ ቢዝነስህን Specialize ማድረግ ነው ወይስ Generalize ማድረግ?
በትምህርት አለም ያለህ ብትሆን ወይም የጥበብ ሰው ወይም የሌላ ባለሙያም ብትሆን ይህ ርእስ ይመለከተሃል። እውቀትህን Specialize ማድረግ ነው ወይስ Generalize ማድረግ? የትኛው የበለጠ ውጤታማ ያደርግሃል?
ምን ማለት ነው?
Business Specialization ማለት አምራች ከሆንክ አንድ አይነት ወይም ተመሳሳይ ምርት ላይ ብቻ አተኩረህ መስራት ማለት ነው። ገዝቶ ሻጭ ነጋዴም ከሆንክ እንደዛው፡ አንድ ነገር ላይ ማተኮር ማለት ነው። ባለሙያም ከሆንክ በአንድ ሞያ ላይ አተኩረህ በዛ የጠለቀ እውቀት እንዲኖርህ ማድረግ፣ ስትሰራም እንደዛው። በትምህርት ላይ ያለህ ሰው ከሆንክም ትምህርትህን በአንድ ዘርፍ ላይ ማተኮር ማለት ነው።
ለምሳሌ Specialist ሃኪም እና ጠቅላላ ሃኪም ሲባል ሰምተሃል። ጠቅላላ ሃኪም ማለት ህክምናውን በጥቅሉ የተማረ በጥልቀት ባይሆንም ሁሉንም የሚያክም ማለት ሲሆን ስፔሻሊስት ሃኪም ደግሞ በአንድ የህክምና ዘርፍ ላይ በጥልቀት የተማረና በዛ ዘርፍ በጥልቀት መረዳት የሚችል ማለት ነው። የአጥንት ስፔሻሊስት፣ የህጻናት ስፔሻሊስት፣ የቆዳ ስፔሻሊስት፣ …
በንግዱም ብናየው፡ የግብርና ምርቶችን ብቻ የሚነግድ፣ በህንጻ መሳሪያ ንግድ ላይ ብቻ የተሰማራ፣ የኮስሞቲክስ እቃዎች ንግድ ላይ ብቻ ያተኮረ፣ የህጻናት ምግቦችን ብቻ የሚያከፋፍል፣ መድሃኒት አከፋፋይነት ላይ ብቻ የተሰማራ …
በአገልገሎትም ቢሆን እንደዛው ነው። በአንድ ዘርፍ ላይ ብቻ ተሰማርቶ አድምቶ የሚሰራ ማለት ነው።
Business Generalization ማለት ደግሞ በተቃራኒው ያለ ነው። በአንድ ጊዜ በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ላይ መሰማራት፣ የተለያዩ ምርቶችን ማምረት፣ የተለያዩ ሙያዎች ባለቤት መሆን፣ የተለያዩ የትምህርት ዘርፎችን ማጥናት …
ለምሳሌ አንድ ሰው ወይም አንድ ኩባኒያ በአንድ ጊዜ የተለያዩ ምርቶችን የሚያመርት፣ የሚያስምጣ፣ ግብርና ላይ የተሰማራ፣ እንደ ሆቴልና ካፊቴሪያ ያሉ አገልግሎት ሰጪ ስራዎች ላይ የተሰማራ ሊሆን ይችላል።
ባለሙያም ከሆነ በአንድ ጊዜ የኤሌክትሪክ ባለሙያም፣ የቧንባ ሰራተኛም፣ የIT ባለሙያም … ወዘተ ሊሆን ይችላል።
አንድ ሰው ሃኪምም፣ ፖለቲከኛም፣ ነጋዴም … ሊሆን ይችላል።
በአንድ ጊዜ ደራሲም፣ ሰአሊም፣ የህግ ባለሙያም፣ … ወዘተ ሊሆን ይችላል።
አሁን ጥያቄው፡ የበለጠና በተሻለ ፍጥነት ውጤታማ የሚያደርግ፣ ትልቅ ደረጃ የሚያደርሰው መንገድ የቱ ነው? የሚል ይሆናል?
Business Specialization ወይስ Business Generalization? በአንድ ነገር ላይ አተኩሮ አድምቶ መስራት ወይስ የተለያዩ አማራጭ ስራዎች ላይ በአንድ ጊዜ መሰማራት?
የሁለቱም መንገዶች ጥቅምና ጉዳታቸው በሰፊው በተከታታይ እንተነትናለን። እስከዛው በነዚህ ጉዳዮች ላይ ያላችሁን አስታያየትና ምልከታ ከስር ባለው ኮሜንት መስጫ ላይ ጻፉልን። ለተሳትፎአችሁ እናመሰግናለን።
© ሙስጦፋ አብደላ
በ0929296992 ደውሉ።


Add a Comment