360_F_313467781_CLyVsc3GffbrSRlXqBc0Qs4utL5wmwHo

Mastermind Group

Mastermind Group ምንድነው?

Mastermind Group ማለት ሰዎች አንድ ላይ እየተገናኙ የሚተጋገዙበት፣ አንዱ አንዱን የሚያበራታታበት፣ ከአንዱ ልምድ ሌላው የሚማርበት ለተመሳሳይ የጋራ ወይም የየግል ህልም ስኬት በጋራ የሚሰሩበት  በተመሳሳይ የአስተሳሰብ ኢነርጂ ላይ ያሉ ሰዎች ስብስብ ነው።

Mastermind Group ምንድነው የሚሰራው?

የ Mastermind Group ተመሳሳይ አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች የአቻ ድጋፍን እንዲያገኙ፣ ሃሳቦችን እንዲያስቡ እና በትግበራ ላይ በሃሳብ እብዲተጋግዙያግዛል። ማስተርማይንድ ግሩፖች በተለምዶ ግብ ላይ ያተኮሩ (goal-oriented) እና ለስኬት የሚጓዙ (success-driven) ናቸው። Mastermind ቡድኖች እንደ የግል የዳይሬክተሮች ቦርድ ወይም እንደ አማካሪ ቦርድ ሊያገለግሉ ይችላሉ።
የ Mastermind Group ዋና ጠቀሜታ ምንድን ነው?
የ Mastermind Group አላማ የቡድኑ አባላት እርስ በርሳቸው በመመካከር በሃሳብ በመድጋገፍ ችግሮችን መፍታት እና በጋራ ማደግ እንዲችሉ ነው። የMastermind Group እሴት የኢነርጂ ጥምረት (synergy of energy) ፣ ተነሳሽነት( motivation) እና ቁርጠኝነት (commitment) እንዲሁም አብሮ ለመማር እና ለማደግ ያለው ፍላጎት ነው።
የ Mastermind Group የራስ ስብዕና ለመገንባትም ሆነ ንግድን ለማሳደግ እንዲሁም ህልምን ለማሳካት በእጅጉ የሚጠቅም መድረክ ነው።

ኦፕራ ዊንፍረይ እንዲህ ትላለች።

“Surround yourself with people who are going to lift you higher.”

“ወደ ከፍታ ለመውጣት የሚያግዙህን ሰዎች በዙሪያህ አሰባስብ።”
 የ Mastermind Group ጽንሰ-ሀሳብ በመጀመሪያ ያስተዋወቀው ናፖሊዮን ሂል ነው። Think and Grow Rich (1937) በተሰኘው መጽሐፉ ማስተርማይድን ቢያንስ የሁለት ሰዎች ስብስብ አድርጎ ይገልጽ እና ችግሮችን የመፍታት ዓላማ ይዘው ይሰባሰባሉ ይላል። የናፖሊዮን ሂል ግኝቶች በዋነኛነት በወቅቱ የማስተር ማይንድ ቡድን የነበራቸውና ስኬታማ የነበሩ የአሜሪካ ኩባንያዎችን በማጥናት ላይ የተመሰረተ ነበር።
ናፖሊዮን ሂል እንዲህ ይላል፡
“ሁለት ሰዎች በማስተር ማይንድ ግሩፕ ሲሰባሰቡ ሦስተኛ የማይዳሰስ ግን ኃይል ያለው አእምሮ ይፈጥራሉ። ይህንን ብቃት ያለው የማይዳሰስ አእምሮ ማስተርማይንድ ተብሎ ይጠራል።”
የMastermind ቡድን ውበቱ ሁሉም አባላት ግቦችን ለመፍጠር እና ለመተግበር ፣ሀሳቦችን ለማንፀባረቅ እና በፍፁም ታማኝነት ፣በመከባበር እና በመተሳሰብ እርስ በእርስ ለመደጋገፍ፣ እርስ በእርስ ቻሌንጅ በመደራረግ መድረኩን ከፍ ማድረግ ሲችሉ ነው።
 የማስተርማይንድ ቡድኖች ዓይነቶች እና ግቦች
የማስተር ማይንድ ግሩፕ ሲቋቋም አደረጃጀቱና ዓላማው ሊለያይ ይችላል።  የተለያዩ ግቦች እና ውጤቶች ሊኖራቸው የሚችሉ በርካታ መንገዶች አሉ።
ለምሳሌ ግቡ የእያንዳንዱ ግለሰብ ስኬት ወይም በቡድኑ ውስጥ ያሉ ሁሉም ሰዎች የጋራ ስኬት ሊሆን ይችላል።
የማስተርማይንድ ግሩፕ ከሚከተሉት ውስጥ አንዱን ታስቢ አድርጎ ሊቋቋም ይችላል።
• አዳዲስ ሀሳቦችን ማፍለቅ እና ማሰባሰብ
• መማማር
• የቡድን ድጋፍ
• የግል ክህሎቶችን ማሻሻል
• የንግድ ችሎታን ማሻሻል
ወዘተ.

© ሙስጦፋ አብደላ
Tags: No tags

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *