- Challenge ምንድን ነው? እና የፅንሰ–ሃሳቡ ታሪካዊ መሰረትስ ምንድን ነው?
Challenge ማለት በተወሰነ የጊዜ ገደብ ውስጥ የተለየ ግብ ለመድረስ የሚደረግ የተዋቀረ ቁርጠኝነት ሲሆን፣ ብዙ ጊዜ ከ comfort ዞንህ እንድትወጣ የምትገደድበት ነው። ብዙ ቻሌንጆች የ90 ቀናት የጊዜ ማዕቀፍ የሚደረግባቸው በተለይ የሚጨበጥ ለውጥ ለመፍጠር በቂ ጊዜ የሚሰጥ እና ትኩረትህና ተነሳሽነትህ ሳይቀዘቅዝ ለማቆየትም የሚያስችል ብዙም ያላጠረ ብዙም ያልረዘመ ጊዜ ስለሆነ ነው።
የተቀናጀ የራስ ማሻሻያ Challenge ጥልቅ ታሪካዊ ስሮች አሉት፡-
- እንደ ስቶይሲዝም ያሉ ጥንታዊ የፍልስፍና ትውፊቶች በዲሲፕሊን የተደገፈ የራስ ማሻሻያ ልምምዶች ላይ ትኩረት ያደርጉ ነበር። ሴኔካና ሌሎች ስቶይኮች ጥንካሬንና ምስጋናን ለመገንባት መደበኛ የChallenge ዘመቻዎችን ያደርጉ ነበር።
- ዘመናዊ የPersonal Development ቻሌንጆች በ20ኛው ክፍለ ዘመን ከSelf-Help ጽንሰሃሳቦች መነሳት እና ከነዚህ ጋር በተያያዙ የማሻሻያ ፕሮግራሞች መቀጣጠል ጋር ጉልህ ጉልበት አገኙ። የናፖሊዮን ሂል “Think and Grow Rich” (1937) ወደ ተለዩ ግቦች የሚደረግ የተማከለ ጥረትን አስፋፍቷል።
- የ90 ቀናት የጊዜ ማዕቀፍ በተለይ የተለመደው በ1970ዎቹ ዓመታት እንደ Objectives and Key Results (OKRs) ባሉ የማኔጅመንት ንድፈ ሀሳቦች ላይ የሩብ ዓመት የስራ ዑደቶችን ማቀድ ላይ ትኩረት ማድረግ ከተጀመረ በኋላ ነው።
- በራስ ላይ Challenge የመጀመር ጥቅም ምንድን ነው?
በራስ የሚጣሉ ቻሌንጆች በጥናት የተደገፉ ብዙ ጥቅሞች አሏቸው፡-
- የነርቭ ሥርዓት እንደገና መዋቀር (Neurological rewiring) ፡ ምርምሮች እንደሚያሳዩት አዳዲስ ባህሪያትን ከ66-90 ቀናት ለሚያክል ጊዜ ልምምድ ማድረግ ዘላቂ የአእምሮ ውቅር መፍጠር ይችላል፣ ይህም Positive Habits (አዎንታዊ ልማዶችን) በቀላሉ የሚደረጉ (more automatic እንዲሆኑ) ያደርጋቸዋል።
- የሚለካ ለውጥ የሚያመጣ ተነሳሽነት፡ በ90 ቀናት ማዕቀፍ ውስጥ ያሉ አጭር ግቦች አውቶማቲክ ግብረመልስ እና የተነሳሽነት ማነቃቂያ ያመጣሉ።
- የራስን ብቃት ማሳደግ፡ አስቸጋሪ ግቦችን በተሳካ ሁኔታ መጨረስ በሌሎች የሕይወት ዘርፎች ላይም ተጽዕኖ የሚያሳድር ለውጥ የመፍጠር ችሎታን ያሳድጋል።
- ተራራዎችን ተሻግሮ ማለፍ፡ የተጠኑ ቻሌንጆች ብዙውን ጊዜ የእድገትና የለውጥ ማነቆ ከሆነው የምቾት ዞን (Comfort Zone) እንድትወጣ ያሻግርሃል።
- የተሻለ ትኩረት፡ በጊዜ የተገደ Challenge “የጊዜ የለም” ስሜት (sense of urgency) ይፈጥራል:: ስለዚህም ዋናው ግብ ላይ ብቻ እንድታተኩር እና አላስፈላጊ መዘናጋቶችን እንድታስወግድ ያግዝሃል።
- ጽናት፡ በ Challenge ወቅት የሚያጋጥሙህ ፈትናዎችን በብቃት መወጣት ወደፊት ለሚያጋጥሙህ ችግሮች በቀላሉ መቋቋም የምትችልበት ሥነ-ልቦናዊ ብርታትን ይገነባልሃል።
- የተሳኩ የ Challenge ታሪኮች
የማይረሱ የ90 ቀናት ስኬታማ ቻሌንጆች፡ ጥቂት ምሳሌዎች፡-
የቢዝነስ ትራንስፎርሜሽን፡ – ሳትያ ናዴላ በ2014 የማይክሮሶፍት ሲኢኦ ሆኖ እንደተመረጠ የድርጅቱን የስራ ባህል ለመቀየር በመጀመሪያዎቹ ቀናት ሁሉን አቀፍ የ90 ቀናት ቻሌንጅ አወጀ። “አድምጥ-ተማር-ምራ” (“listen-learn-lead” ) የሚል መርህን ተግብሮ ማይክሮሶፍትን ወደ ክላውድ አገልግሎቶች እና አካታች ንድፎች ትኩረቱን እንዲያዞር አድርጓል፣ በመጨረሻም የድርጅቱን ጎዳና ቀይሮ የማይክሮሶፍት ኩባንያ ሃብትን በሶስት እጥፍ እንዲያድግ አድርጓል። ይህም የ90 ቀናት ቻሌንጅ ጠቀሜታ ለማስረዳት እንደማጣቀሻ ሆኖ እንዲያገለግል ያስገደደ ታላቅ ስኬት ነበር።
አካላዊ ለውጥ፡ የዶክሜንታሪ ፊልም አዘጋጅ ሞርጋን ስፐርሎክ በ”ሱፐር ሳይዝ ሚ” ፊልሙ ምክንያት ከደረሰበት የሰውነት ውፍረት እና አካላዊ ጉዳት በጥብቅ የ90 ቀናት የምግብ ዳይት እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ቻሌንጅ ሙሉለሙሉ ወደነበረበት ጤንነት እና አካላዊ ሁኔታ መመለስ የቻለበት ፍጥነት እና ስኬት ለብዙዎች ማስተማሪያ ሆኗል።
ጠቃሚ ልማዶችን መገንባት፡ ደራሲ ጄምስ ክሊር “አቶሚክ ሀቢትስ” በሚባለው መጽሐፉ በተለያዩ ግለሰቦች የቀረቡ በርካታ የ90 ቀናት ቻሌንጆችን አካቷል። ከእነዚህም መካከል በ90 ቀናት ቻሌንጅ ብቻ ከአደገኛ ሱስ መላቀቅ የቻሉ፣ ከተወቃሽ ተማሪነት ወደ ተሸላሚነት የተሸጋገሩ ይገኙበታል።
የሙያ እድገት፡ “100 Rejections Challenge” የተሰኘው ቻሌንጅ ብዙ ባለሙያዎች የመውደቅ ፍርሃትን ማሸነፍ እንዲችሉ ረድቷቸዋል። ክ90-100 ለሚሆኑ ቀናት ባካሄዱዋቸው የቻሌንጅ ዘምቻዎች የማይታመን ውጤትን ተጎናጽፈዋል።
By: Mustofa Abdella


Add a Comment